image
image
image
image
image

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የመስሪያ ቦታዎች የሀገርን ኢኮኖሚ በማጠናከር ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸው ተገለጸ።

ሰኔ 16, 2018
‎ከአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት እና ከክፍለ ከተማው ምክር ቤት የተውጣጡ የንግድ ኢንደስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በክፍለ ከተማው በሚገኙ የስራ ቦታዎች ላይ የመስክ ምልከታ አድርገዋል። ‎ ‎የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት የዜና ክፍል እንደዘገበው የጉብኝቱ ዋና ዓላማ የመስሪያ ቦታዎችን ያሉበት ሁኔታ እና በልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ያላቸው ሚና ለመገምገም ነው። ‎ ‎የቋሚ ኮሚቴዎቹ አባላት በምልከታቸው ወቅት የመስሪያ ቦታዎቹ እያስመዘገቡ ያሉትን ዘርፈ ቡዙ አዎንታዊ ውጤቶች ተመልክተው መደሰታቸውን ገልጸዋል። ‎ ‎በክፍለ ከተማው የሚገኙ የመስሪያ ቦታዎች ለአካባቢው ነዋሪዎች ሰፊ የስራ ዕድል መፍጠራቸው በመስክ ምልከታው ወቅት የተገለጸ ሲሆን ተኪ ምርቶችን በማምረት የውጭ ምንዛሬን ማስቀረት ረገድም የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነውም ተብሏል። ‎ ‎በነዚሁ ተቋማት አማካኝነት ለአዳዲስ ሰራተኞች እና ለሌሎች ዜጎች ዕውቀትን ማሸጋገር መቻሉ እና ነዋሪዎች ከአካባቢያቸው ሳይርቁ እዚያው ተረጋግተው እንዲሰሩ በማገዝም ማህበራዊ መረጋጋት እንዲፈጠር ያስቻሉ ስለመሆናቸውም ከጉብኝቱ መረዳት ተችሏል። ‎ ‎በጉብኝቱ ወቅት የነባር የአዲስ እና በግንባታ ላይ ያሉ የመስሪያ ቦታዎች ሁኔታ ታይቷል። ‎ ‎ነባር የሆኑ መስሪያ ቦታዎች ለስራ ምቹ እና ጽዱ በማድረግ እና አዳዲስ የተገነቡ የመስሪያ ቦታዎች ደሞ ዘመናዊ አሰራርን የተከተሉ እና ምርታማነትን ለማሳደግ ታስበው የተገነቡ መሆናቸው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማት ጽ/ቤት በጉብኝቱ ወቅት አሳውቋል። ‎ ‎የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ በስተመጨረሻ እነዚህ ዘመናዊ የመስሪያ ቦታዎች ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ በሀገሪቱ አጠቃላይ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ እና ዘላቂ አስተዋጽዖ እንደሚኖራቸው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ‎የክፍለ ከተማው የመስሪያ ቦታዎች ልማት ጽ/ቤት በበኩሉ እነዚህን የመስሪያ ቦታዎች ለስራ ማመቻችትና ምርታማነትን በመጨመር የአገር ኢኮኖሚ ላይ የበኩላቸውን አስተዋ ማበርከት በሚችሉበት ደረጃ ለማድረስ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውሶ በዚህም አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝ ጨምሮ ገልጿል። ‎

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች